Fana: At a Speed of Life!

የኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ በኢትዮጵያ ከኩዌት አምባሳደር  ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ በኢትዮጵያ ከኩዌት አምባሳደር ናይፍ አል ቃጥቢ ጋር ተወያዩ።

በውይይታቸውም የጋራ የኢንቨስትመንት ማስተዋወቅ ስራ፣ በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ዕድል እና አማራጮች ለኩዌት ባለሃብቶች ማስተዋወቅ ስለሚቻልባቸው መንገዶች መክረዋል።

ከዚህ ባለፈም የሁለቱን ሀገራት ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል።

አምባሳደር ናይፍ በበኩላቸው የሁለቱን ሀገራት ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ለማጠናከር፣ በኢትዮጵያ ያሉ የኢንቨስትመንት ዕድል እና አማራጮችን ለኩዌት ባለሀብቶች በማስተዋወቅ ባለሃብቶችን ወደ ኢትዮጵያ ለመሳብ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.