Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ በበጎ ፈቃድ የሚገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ መርሐ ግብር በይፋ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጀርመን በኢትዮጵያ ማህበራዊ ዋስትና እንዲረጋገጥ እና ሀገሪቱ ከግጭት እንድታገግም የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል አስታወቀች፡፡

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ በጀርመን ኢኮኖሚ ትብብርና ልማት ሚኒስትር የአፍሪካ ዳይሬክተር ቢሪግት ፒከል ከተመራ ልዑክ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱ ሁለቱም ወገኖች ከግጭት በኋላ ሊደረጉ በሚችሉ የተሃድሶ እና የመልሶ ግንባታ ስራዎች ላይ የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ተሳትፎን በተመለከተ ምክክር አድርገዋል፡፡
በተጨማሪም በኢፌዴሪ መንግስት እና በህወሓት መካከል ስለተደረሰው የሰላም ስምምነት እና በሀገራቱ የልማት አጋርነት ዙሪያም መክረዋል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ የኢትዮጵያ መንግስት የሰላም ስምምነቱን በፍጥነት ተግባራዊ ለማድረግ እና ተጨባጭ ውጤቶችን ለማሳየት ቁርጠኛ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው ገልጸዋል።

በጀርመን ኢኮኖሚ ትብብር እና ልማት ሚኒስትር የአፍሪካ ዳይሬክተር ቢሪግት ፒከል በበኩላቸው፥ የተደረሰውን የሰላም ስምምነት አድንቀው ለዘላቂ ሰላም ለሚደረገው ጥረት አጋዥ መሆኑን አስረድተዋል።

አያይዘውም የሰላም ስምምነቱ ዋጋ እንዲታወቅ መሰረታዊ አገልግሎቶችን ወደነበሩበት መመለስ፣ ሰብአዊ ድጋፍ ተደራሽነትን ማረጋገጥ እና ተጠያቂነትን ማስፈን አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ጀርመን ኢትዮጵያን ለመደገፍ ለሴፍቲ ኔት ከምታደርገው የ30 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ በተጨማሪ በግጭት ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎችና ለግጭት ማገገሚያ የሚውል 15 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብታለች፡፡

በተጨማሪም ጀርመን በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች የሚውልና በዓለም አቀፉ የምግብ ፕሮግራም እና ዓለም አቀፉ የህጻናት መርጃ ድርጅት በኩል ለሚደረገው እርዳታ ማስፈጸሚያ እንዲሁም የምግብ ዋጋ ግሽበትን ለማረጋጋት የሚውል የ30 እና 35 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ እንደምታደርግም አስታውቃለች።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.