Fana: At a Speed of Life!

በአፋር ክልል በጦርነቱ ለተጎዱ ዜጎች የ170 ሚሊየን ብር ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር በአፋር ክልል በጦርነቱ ለተጎዱ ዜጎች የ170 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል።

ሚኒስቴሩ በከተማ ሴፍቲኔት መርሐ ግብር በከተሞች ከሚያደርገው ድጋፍ ባለፈ በአሽቸኳይ አደጋ ምላሹ ነው ድጋፉን ያደረገው።

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ÷ ድጋፉ ለተጎጂዎች በቀጥታ እንዲደርስ ክልሉ ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራ አስገንዝበዋል።

ተጨማሪ ሀብቶችን በማሰባሰብ መሰል ድጋፎችን ሚኒስቴሩ እንደሚያደርግም አመላክተዋል፡፡

የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በበኩላቸው÷ ተቋሙ ከዚህ በፊትም ድጋፎችን በክልሉ ተገኝቶ ሲያደርግ እንደነበር አስታውሰው ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

በወንድሙ አዱኛ

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.