Fana: At a Speed of Life!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች የ590 ሚሊየን ብር ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 9 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ ለተፈናቀሉ ዜጎች የ590 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ ለቤኒሻለንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን አስረክበዋል፡፡

ሚኒስቴሩ በአፋጣኝ የአደጋ ምላሽ መርሐ ግብሩ ለክልሉ ያደረገው ድጋፍ በከተሞች ያለውን ጫና የሚቀርፍ ነው ተብሏል።

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ ድጋፉ ለተጎጂዎች በቀጥታ እንዲደርስ የክልሉ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራ አስገንዝበዋል።

የቤኒሻለንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን በበኩላቸው÷ ለከተሞች እድገትና ለተፈናቃዮች ሚኒስቴር መስሪያቤቱ እያደረገ የሚገኘው ድጋፍ የሚደነቅ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ለተደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን ያቀረቡት ርዕሰ መስተዳድሩ ÷ድጋፉ ለታለመለት ዓላማ እንዲውል የተቀናጀ ክትትል እንደሚደረግ አረጋግጠዋል።

ድጋፉ በክልሉ በተለያዩ ምክንያቶች የተፈናቀሉ ከ107 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በወንድሙ አዱኛ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.