Fana: At a Speed of Life!

ሰሜን ኮሪያ አሜሪካን የመምታት ዐቅም አለው የተባለለትን አኅጉር አቋራጭ ሚሳኤል አስወነጨፈች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሜን ኮሪያ አሜሪካን የመምታት ዐቅም አለው የተባለለትን አኅጉር አቋራጭ ባላስቲክ ሚሳኤል ማስወንጨፏን የጃፓን መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሰሜን ኮሪያ ዛሬ ያስወነጨፈችው ሚሳኤል÷ በጃፓን ሰሜናዊ ክፍል ከምትገኘው ሆካይዶ ደሴት በስተምዕራብ 210 ኪሎ ሜትሮች ራቅ ብሎ ባሕር ውስጥ መውደቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በባንኮክ እየተካሄደ ከሚገኘው የእስያ-ፓሲፊክ የኢኮኖሚ ትብብር መድረክ ጎን ለጎን ስለ ጉዳዩ ለጋዜጠኞች መግለጫ መስጠታቸውን ጃፓን ታይምስ ዘግቧል፡፡

ሰሜን ኮሪያ በፈረንጆቹ ሕዳር 3 ላይ ለሙከራ በሚል አከታትላ የተኮሰቻቸው ከ23 በላይ አኅጉር አቋራጭ ሚሳኤሎች ደቡብ ኮሪያን ጨምሮ ቀጣናውን ሥጋት ላይ መጣሉን ኤን ቢሲ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

በወቅቱ የወጡ መረጃዎችም አኅጉር አቋራጭ ሚሳኤሉ አሜሪካን ጭምር የመምታት ዐቅም እንዳለው አመላክተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.