Fana: At a Speed of Life!

በሙሉ አቅም ማምረት አለመቻሉ እና የፍላጎት መጨመር የሲሚንቶ እጥረት እንዲከሰት ማድረጉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሁኑ ወቅት ለተከሰተው የሲሚንቶ ምርት እጥረት በሙሉ አቅም ማምረት አለመቻሉ እና የፍልጎት መጨመር መንስኤ መሆናቸውን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

የሲሚንቶን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባም ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡

ሚኒስቴሩ ከሲሚንቶ አምራቾች ጋር ተወያይቷል፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ገብረመስቀል ጫላ በውይይቱ ላይ እንደገለጹት÷ እንደ ሀገር በአሁኑ ወቅት በሲሚንቶ አቅርቦት ላይ እየተስተዋለ ያለውን ችግር ለመቅረፍ በትኩረት መሥራት ይገባል፡፡

የአምራቾችን፣ የነጋዴዎችን ብሎም የተጠቃሚውን አንጻራዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሲሚንቶ ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን መፍታት ተገቢ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት እየተስተዋለ ላለው የሲሚንቶ እጥረት መንስኤው የሲሚንቶ ማምረቻ ተቋማት በሙሉ አቅማቸው እያመረቱ አለመሆኑ ነው ብለዋል፡፡

ችግሩን ለመቅረፍም ሚኒስቴሩ ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሠራ ገልጸዋል፡፡

የንግድ ሥርዓትና ላይሰንሲንግ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ በልሁ እንደገለጹ÷ በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ ለተከሰተው የሲሚንቶ እጥረት ሌላኛው መንስኤ የፍላጎት በእጥፍ መጨመር ነው ማታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

የሲሚንቶ ምርት የኮንትሮባንድ እና የሙስና ምንጭ ሊሆን ስለሚችል ዘርፉ በጥንቃቄ እና በጥሩ ሥነ ምግባር መመራት እንደሚገባው በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.