Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በ3ኛው የፀረ ሽብር ፋይናንስ የሚኒስትሮች ኮንፈረንስ ላይ እተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 10 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰላም ሚኒስትሩ አቶ ብናልፍ አንዱአለም የሚመራ ልዑክ ቡድን በህንድ ኒው ደልሂ እየተካሄደ ባለው 3ኛው የፀረ ሽብር ፋይናንስ የሚኒስትሮች ኮንፈረንስ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።

ኮንፈረንሱ ”ለሽብር የሚውል ገንዘብ የለም ” በሚል መሪ ሃሳብ ከህዳር 9 ቀን ጀምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት እየተካሄደ ይገኛል።

የሰላም ሚኒስትሩ አቶ ብናልፍ በኮንፈረንሱ ላይ ባደረጉት ንግግር የኢትዮጵያ መንግስት ሽብርተኝነትን እና ዓለም አቀፍ አሸባሪ ቡድኖችን በመዋጋት የሀገሪቱን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በዓለም አቀፍ እና በሀገር ደረጃ የሚደረጉ የሽብር ተግባራትን ለመከላከል እና ህገወጥ የፋይናንስ ግብይቶችን እና የገንዘብ ዝውውርን ለመዋጋት የመንግስት ተቋማትና የፋይናንስ መረጃ ማዕከላት ያላቸውን ሚና በተመለከተም አብራርተዋል።

ሽብርተኝነት ዓለም አቀፍ ስጋት መሆኑን በመረዳት ተቋማዊ ሥርዓትን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ የገለፁት አቶ ብናልፍ ኢትዮጵያ በገንዘብ የሚደገፍ ሽብርተኝነትን ለመከላከል ቁርጠኛ ናት ማለታቸውን የሰላም ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.