Fana: At a Speed of Life!

ብቁና ጥሩ ዜጎችን ማፍራት የሚያስችል ሥራ መሥራት እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስትሩ ተናገሩ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 10 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ብቁና ጥሩ ዜጎችን ማፍራት የሚያስችል ሥራ መሥራት ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ለሦስት ቀናት በሐዋሳ ከተማ ሲካሄድ የቆየው 31ኛው የትምህርት ጉባኤ በተሳታፊዎች ባለ 8 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል።

በማጠናቀቂያው ላይ መልዕክት ያስተላለፉት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ፥ የአንድ ቢሮ ኃላፊ ወይም ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ኃላፊነት ብቁና ጥሩ ዜጎችን ማፍራት የሚያስችል ሥራ መሥራት መሆኑን በመረዳት ኃላፊነትን መወጣት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

አክለውም የትምህርት ሥርዓቱ ላይ ያሉ ችግሮችን በተናጥል በሚደረግ ጥረት መፍታት እንደማይቻል ጠቅሰው፥ ለዚህም ሁሉም በሚችለው ልክ ዘርፉን እንዲደግፍ ጥሪ አቅርበዋል።

በጉባኤው የትምህርት ጥራትን ለማረገገጥ፥ ብቁ እና ተወዳዳሪ የሰው ሀይል ማፍራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች መግባባት ላይ መደረሱን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

በተጨማሪም ባለድርሻ አካላትን በማሣተፍ ምቹ የትምህርት ቤት አካባቢን በመፍጠር የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ማሻሻል እንደሚገባ ተገልጿል።

በሌላ በኩል በመድረኩ የ2014 ዓም የ12ኛ ክፍል ፈተና በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት እውቅናና ሽልማት የተሰጠ ሲሆን÷በማጠናቀቂያ ፈተናው የተደረገው ጥንቃቄን ጨምሮ የተሰጠበት ሂደት ለቀጣይ መነሻ የሚሆን እና በስኬት የተነሳ ነው።

በፈተናውም 32 ሺህ የሚደርሱ አስፈፃሚዎች መሳተፋቸውም ተገልፆ በዚህም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ የክልል ትምህርት ቢሮዎች፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ፣ የፀጥታ ተቋማት እንዲሁም የየአካባቢው ማህበረሰብ ከፍተኛ ርብርብ ማድረጋቸው ተገልጿል።

በመድረኩ ቀጣይ ሊስተካከሉ የሚገባቸው ጉዳዮች ተነስተው ውይይትም ተካሂዶባቸዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ÷ የታየው የቅንጅት ስራ የሚደነቅና የሚመሰግን መሆኑን በማንሳት ከዚህም በኋላ ኩርጃን የማስቀረት አካሄድ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ለተወሰደው ከፍተኛ ሃላፊነትና የተቀናጀት ስኬት አስተዋፅኦ ላደረጉ ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በሀብታሙ ተ/ስላሴ ተጨማሪ መረጃ የትምህርት ሚኒስቴር

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.