Fana: At a Speed of Life!

የዘንድሮውን ታላቁ ሩጫ በወንዶች አትሌት አቤ ጋሻው ለሦስተኛ ጊዜ አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዘንድሮውን ታላቁ ሩጫ በወንዶች ከአማራ ማረሚያ ቤት አትሌት አቤ ጋሻው አሸንፏል፡፡

አትሌት አቤ ጋሻው የዘንድሮውን ሲያሸንፍ ለሦስተኛ ጊዜ መሆኑን ተናግሯል፡፡

አትሌት ኃይለማርያም አማረ ከፌደራል ማረሚያ ሁለተኛ እና አትሌት ገመቹ ዲዳ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ የዘንድሮውን ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አጠናቀዋል፡፡

በተመሳሳይ በሴቶች የተካሔደውን ውድድር ከኦሮሚያ ደን ጥበቃ ኢንተርፕራይዝ አትሌት ትዕግስት ከተማ አንደኛ፣ ከአዲስ አበባ ፖሊስ መስታወት ፍቅሩ ሁለተኛ እና ከንግድ ባንክ ፎይቴን ተስፋዬ ሦስተኛ በመሆን አጠናቀዋል፡፡

በውድድሩ አንደኛ ለወጡት አትሌት አቤ ጋሻው እና ትዕግስት ከተማ እያንዳንዳቸው የ150 ሺህ ብር ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

በአምባሳደሮች ዘርፍ በሴቶች የተካሔደውን ውድድር በኢትዮጵያ የፊንላንድ አምባሳደር፣ በአውሮፓ ሕብረት የኢትዮጵያ አምባሳደር እና በኢትዮጵያ የአየርላንድ አምባሳደር በቅደም ተከተላቸው መሰረት ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል፡፡

በአምባሳደር ዘርፍ ተወዳድረው ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ለወጡት ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.