Fana: At a Speed of Life!

በማራቶን ሪሌይ ውድድር የኦሮሚያ ፖሊስ አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሠመራ ከተማ በተካሔደው 18ኛው የኢትዮጵያ ማራቶን ሪሌይ ውድድር ኦሮሚያ ፖሊስ አሸንፏል፡፡

በክለቦች መካከል በተካሔደው የማራቶን ሪሌይ ውድድር÷ የኦሮሚያ ፖሊስ አንደኛ በመሆን የወርቅ ሜዳሊያና የገንዘብ ተሸላሚ ሆኗል፡፡

በዚሁ የውድድር መርሐ ግብር ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ገንዘብና ሜዳሊያ ተሸልሟል፡፡

ሦስተኛ ደረጃን ይዞ ውድድሩን ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የገንዘብና የነሐስ ሜዳሊያ መሸለሙን የአትሌቲክስ ፌደሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

የኦሮሚያ ፖሊስ አትሌቲክስ ክለብ የአጠቃላይ የአሸናፊ ዋንጫ ሽልማትን ከዕለቱ የክብር እንግዶች ተቀብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.