
ቦሪስ ጆንሰን በኮሮና ቫይረስ ተያዙ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 18 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሪታንያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን በኮሮና ቫይረስ ተያዙ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተደረገላቸው ምርመራ የቫይረሱን ምልክት ማሳየታቸውን በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ አስታውቀዋል።
ቦሪስ ጆንሰን አሁን ላይ ራሳቸውን ማግለላቸውንም ነው ያስታወቁት።
የመንግስት ስራዎችንም በቪዲዮ ኮንፈረንስ እንደሚመሩም ገልጸዋል።
ምንጭ፦ ሲ ኤን ኤን
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision