በሦስተኛው ቀን የዓለም ዋንጫ ውሎ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሦስተኛ ቀኑን በያዘው 22ኛው የዓለም ዋንጫ ዛሬ አራት ጨዋታዎች ይካሔዳሉ፡፡
በምድብ ሦስት የተደለደለችው አርጀንቲና ቀን 7 ሰአት ላይ ከሳዑዲ ዓረቢያ ጋር ትጫወታለች፡፡
ሊዮኔል ሜሲ የመጨረሻው በሆነው የዓለም ዋንጫ ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር በድል ለመመለስ ዛሬ አንድ ብሎ ይጀምራል።
በዚሁ ምድብ የደለደሉት ሜክሲኮ እና ፖላንድ ምሽት 1 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያከናውናሉ፡፡
በምድብ አራት ደግሞ አፍሪካዊቷ ቱኒዚያ ከዴንማርክ ጋር ከቀትር በኋላ 10 ሰዓት ላይ ጨዋታዋን ታደርጋለች።
በዚሁ ምድብ ወሳኝ ተጫዋቾቿን በጉዳት ያጣችው ፈረንሳይ ከአውስትራሊያ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ትጫወታለች።
በኳታሩ የዓለም ዋንጫ እስካሁን አራት ጨዋታዎች ተደርገው በመሸናነፍ የተጠናቀቁ ሲሆን፥ 14 ጎሎች ደግሞ ከመረብ አርፈዋል።
ትናንት አመሻሽ እንግሊዝ ከኢራን ያደረጉትና በእንግሊዝ 6 ለ 2 አሸናፊነት የተጠናቀቀው ጨዋታ በውድድሩ በርካታ ጎሎች የተስተናገደበት ሆኗል።