Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ የሁለት ሕጻናት ሕይወት በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲያልፍ አድርጋለች በተባለችው ተከሳሻ ላይ የጥፋተኝነት ፍርድ ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁለት ሕጻናትን በአሰቃቂ ሁኔታ ሕይወታቸው እንዲያልፍ አድርጋለች የተባለችው ሕይወት መኮንን ላይ የጥፋተኝነት ፍርድ ተሰጠ፡፡

ተከሳሽ በለሚኩራ ክፍለ ከተማ በቤት ሠራተኛነት ተቀጥራ በምትሠራበት መኖሪያ ቤት ውስጥ፥ የሁለት ሕጻናትን ሕይወት በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲያልፍ አድርጋለች በሚል በከባድ የግድያ ወንጀል እና የሟቾችን የቤተሰብ ሰነድ ማስረጃዎች ማጥፋት ወንጀል ተደራራቢ ክስ ተመስርቶባት ነበር፡፡

ተከሳሽ ወንጀሉን አልፈጸምኩም በማለት ክዳ የተከራከረች በመሆኑ ዐቃቤ ሕግ ተከሳሽ ወንጀሉን መፈጸሟን ያስረዳሉ ያላቸውንሥድስት የሰው ምስክሮችን አቅርቦ ለችሎቱ ማሰማቱን፣ ችሎቱም መርምሮ በጉዳዩ ላይ ብይን ለመስጠት ለዛሬ ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር።

ጉዳዩን የተመለከተው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ሰው ግድያና ከባድ ውንብድና ወንጀል ችሎት፥ ተከሳሽ በተከሰሰችባቸው ተደራራቢ ክሶች እንድትከላከል ብይን ቢሰጥም የመከላከያ ማስረጃ የለኝም በማለቷ የመከላከል መብቷ ታልፎ ፍርድ ቤቱ ዐቃቤ ሕግ ክሱን በማስረጃ በማረጋገጡ ተከሳሽን ጥፋተኛ በማለት ፍርድ ሰጥቷል፡፡

ፍርድ ቤቱም ቅጣት ለመወሰን ለሕዳር 26 ቀን 2015 ዓ.ም ቀጠሮ መስጠቱን የፍትሕ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.