Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ ፌሪስ የባሕር ትራንስፖርት ድርጅት ተመሰረተ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት እና ጣና ሐይቅ ትራንስፖርት ድርጅት ተዋህደው ኢትዮ-ፌሪስ የባሕር ትራንስፖርት ድርጅትን መሰረቱ፡፡

የድርጅቶቹ የውህደት ይፋ ማድረጊያ እና የኢትዮ ፌሪስ የባሕር ትራንስፖርት ድርጅት ምስረታ ሥነ ስርዓት በባሕርዳር ከተማ ተካሂዷል፡፡

በመርሐ ግብሩ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ እና የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሮባ መገርሳን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ በሥነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ኢትዮ ፌሪስ የባሕር ትራንስፖርት ድርጅት መመሥረቱ በጣና ሐይቅ ላይ ለህብረተሰቡ እና ለጎብኚዎች የሚሰጠውን አገልግሎት ተወዳዳሪ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

አቶ ሮባ መገርሳ እንደገለጹት ኢትዮ ፌሪስ የባሕር ትራንስፖርት ሁለገብ ዘመናዊ ሕንፃ ግንባታን ጨምሮ የትራንስፖርት፣ የጭነት እና ልዩ አገልግሎት የሚሰጡ ጀልባዎችን ከማስመጣት ጀምሮ በርካታ የለውጥ ሥራዎች ለማከናወን ያግዛል፡፡

የጣና ሐይቅ ትራንስፖርት ድርጅት በ1942 ዓ.ም የተመሠረተ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ድርጅት ነው።

ውህደቱ ሁለቱ ድርጅቶች በቅንጅት የሚሠሩበት መሆኑ ተገልጿል፡፡

በሳሙኤል ወርቃየሁ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.