Fana: At a Speed of Life!

ቱርክ የኩርድ አማፂያን ይገኙባቸዋል ባለቻቸው 500 ያህል ዒላማዎች ላይ ጥቃት ፈጸመች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቱርክ በኢራቅ እና በሶሪያ በሚንቀሳቀሱ የኩርድ አማፂያን ላይ ባካሄደችው የዓየር ጥቃት 500 የሚጠጉ ዒላማዎችን መምታቷን አስታወቀች፡፡

ቱርክ በቅርቡ ባካሄደቻቸው የዓየር ጥቃቶች አማፂዎቹ መሽገውባቸዋል ያለቻቸውን 471 ዒላማዎች መምታቷን አስታውቃለች፡፡

በወሰደችው ወታደራዊ እርምጃም 254 አማፂያን መደምሰሷን ሲ ጂ ቲ ኤን አናዱሉን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡

ቱርክ ከዕሑድ ማለዳ ጀምሮ የዓየር ጥቃት ስትፈፅም የቆየችው ራሳቸውን “ዋይ ፒጂ” እና የኩርድ ሰራተኞች ፓርቲ “ፒኬኬ” ብለው በሚጠሩ በሰሜን ሶሪያ እና በሰሜን ኢራቅ በመሸጉ አማፂያን ላይ ነው ተብሏል፡፡

በዛሬው ዕለትም “ቱርክ የራሷን ችግሮች በራሷ የመፍታት መብት አላት” ሲሉ በአማፂያኑ ላይ ያላቸውን አቋም የቱርኩ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይፕ ኤርዶኻን ማስታወቃቸውን የተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል፡፡

በዓየር ብቻ ሳይሆን በምድርም ጭምር ጥቃት ሊሰነዝሩ እንደሚችሉም ነው የጠቆሙት።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.