Fana: At a Speed of Life!

በዛሬው የዓለም ዋንጫ ሁለት የአፍሪካ ሀገራት የሚሳተፉበትን ጨምሮ አራት ጨዋታዎች ይካሔዳሉ

 

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አምስተኛ ቀኑን በያዘው የዓለም ዋንጫ ውሎ ካሜሮን እና ጋና የሚሳተፉበትን ጨምሮ አራት ጨዋታዎች ይከናወናሉ፡፡

በዚሁ መሰረት በምድብ ሰባት የተደለደሉት አፍሪካዊቷ ካሜሮን ከስዊዘርላንድ ቀን ሰባት ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያከናውናሉ፡፡

በዚሁ ምድብ የተደለደሉት ብራዚል እና ሰርቢያ ምሽት አራት ሰዓት ላይ ይጫወታሉ፡፡

በሌላ የጨዋታ መርሐ ግብር በምድብ ስምንት የተደለደሉት ዑራጋይ እና ደቡብ ኮሪያ 10 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

በተመሳሳይ በዚሁ ምድብ የሚገኙት ፖርቹጋል እና አፍሪካዊቷ ጋና ምሽት አንድ ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን እንደሚያከናውኑ የወጣው መርሐ ግብር ያመላክታል፡፡

ትናንት በተካሔዱ የዓለም ዋንጫ አራት ጨዋታዎች ሞሮኮ ከክሮሺያ ያለምንም ጎል በአቻ ውጤት ሲለያዩ÷ ጃፓን ጀርመንን 2 ለ1፣ ስፔን ኮስታሪካን 7 ለ 0 እንዲሁም ቤልጂየም ካናዳን 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፋቸው ይታወሳል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.