Fana: At a Speed of Life!

ቤቶች ኮርፖሬሽን የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤትን ከ269 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ለማዘመን ስምምነት ፈረመ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ሕንጻን ለማደስና ለማዘመን የሚያስችለውን ስምምነት ፈረመ፡፡

ስምምነቱን የፈረሙት፥ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ረሻድ ከማል እና የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና ዳይሬክተር መሰረት ዳምጤ ናቸው፡፡

ባለ 10 ወለሉን የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ሕንጻ የማደስና የማዘመን ሥራው በሁለት ምዕራፎች የሚከናወን ሲሆን፥ የመጀመሪያውን ዙር የእድሳት ሥራ በሥድስት ወራት ውስጥ ለማጠናቀቅ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

በአጠቃላይ ሥራውን ለማከናወን ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ 269 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር መመደቡን የቤቶች ኮርፖሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በስምምነቱ መሰረት የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ሕንጻን የእድሳት ሥራ፣ የቴክኖሎጂ መሰረት ልማቶችን ጨምሮ ሙሉ ዲዛይን እና የግንባታ ሥራ ያከናውናል፡፡

አቶ ረሻድ ከማል÷ “የእድሳት እና የማዘመን ሥራውን በተያዘለት በጀት፣ የጥራት ደረጃ እና ጊዜ አጠናቀን እናስረክባለን” ብለዋል፡፡

ወይዘሮ መሰረት ዳምጤ በበኩላቸው፥ “ኮርፖሬሽኑ ለጥራትና ጊዜ ከፍተኛ ትኩረት እንደሚሰጥ ስላረጋገጥን የሥራ ስምምነት አድርገናል” ነው ያሉት።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.