Fana: At a Speed of Life!

ቢሮው የተለያዩ የመስሪያ ቦታዎችን ለተጠቃሚዎች በዕጣ አስተላለፈ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሥራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የተለያዩ የመስሪያ ቦታዎችን ለተጠቃሚዎች በዕጣ አስተላልፏል፡፡

ቢሮው ከዚህ በፊት በተለያየ ምክንያት አገልግሎት ያልሰጡ፣ በህገ ወጥ መንገድ የተያዙ እና ለተጠቃሚ ተላልፈው ለአምስት ዓመታት አገልግሎት የሰጡ የመስሪያ ቦታዎችን ነው ለተጠቃሚዎች ያስተላለፈው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የሥራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ÷ መዲናዋ በርካታ ስራ አጥ ወጣቶች የሚገኙባት እንደመሆኗ መንግስት ስትራቴጂ በመንደፍ የመስሪያ ቦታዎችን ገንብቶ ማስተላለፍን ጨምሮ የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ እንደሆነ ገልጸዋል::

በዚህም÷ 102 ኢንተርፕራይዞች እና 450 አንቀሳቃሾች ተጠቃሚ መሆናቸውን ጠቁመው÷ ከዚህ ውስጥም 55 በመቶ የሚሆኑት ተጠቃሚዎች ሴቶች መሆናቸውን አንስተዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲ ምሩቃን፣ የአካል ጉዳተኞች እና ከስደት ተመላሾች በዕጣው መካተታቸውንም የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢንተርፕራይዞች የሚወስዱትን የመስሪያ ቦታ ከህገ-ወጥ ድርጊት በመቆጠብ በአግባቡ ሊጠቀሙበት እንደሚገባም አቶ ጃንጥራር አሳስበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.