Fana: At a Speed of Life!

26ኛው ጉሚ በለል የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)26ኛው ጉሚ በለል የውይይት መድረክ ” ሕብረ-ብሔራዊ አንድነት ለዘላቂ ሠላም” በሚል ርዕሰ እየተካሄደ ነው።

የውይይት መድረኩ በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ቢሮ ነው እየተካሄደ ያለው፡፡

መድረኩ ከዚህ ቀደምም በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ ውይይት ሲያካሄድበት ቆይቷል።

17ኛውን የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ምክንያት በማድግ የሚካሄደው ይህ መድረክ “ሕብረ- ብሄራዊ አንድነት ለዘላቂ ሠላም ያለው ፋይዳ እና ትሩፋቶቹ ላይ ትኩረቱን አድርጎ ይመክራል ነው የተባለው።

የዘርፉ ምሁራንም በውይይቱ እየተሳተፉ ይገኛሉ ።

በኦሮሞ የፓለቲካ እንቅስቃሴ አንጋፋ የሆኑት አቶ ሌንጮ ለታን ጨምሮ የፌደራሊዝም ጉዳዮች ምሁር ተመሥገን ባይሳ የውይይት መነሻ ፅሁፍ እያቀረቡ ነው።

በሐብታሙ ተ/ሥላሴ

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.