Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን  ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋር እየመከረ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ  ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋር በሚዛን አማን ከተማ እየመከረ ይገኛል፡፡

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽነር ሙሉጌታ  አጎ በመድረኩ ባደረጉት ንግግር ÷ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የህዝብን ፍላጎት ያማከለ ምክክር በሀገሪቱ  በተለያዩ  አካባቢዎች  እያደረገ ስለመሆኑ ገልፀዋል፡፡

ኮሚሽኑ ገለልተኛ በሆነ መልኩ ስራውን በመስራት ላይ ይገኛል  ያሉት ኮሚሽነር ሙልጌታ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ያማረች ሀገርን ለመገንባት እንዲቻል ተሳትፎዉን ሊያሳይ ይገባል ብለዋል፡፡

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ፀጋዬ ማሞ÷ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በህዝቦች መካከል ጥርጣሬን በማስወገድ አብሮነትን የሚያጠናክር ስለመሆኑ ገልፀዋል፡፡

ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ተግባራዊነት እና ውጤታማነትም የክልሉ መንግስት ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

በመድረኩ  የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የዞን እና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች እየተሳተፉ ነዉ፡፡

በተመስገን  ይመር

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.