Fana: At a Speed of Life!

ጉዳት የደረሰባቸው የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን የመጠገን ሥራ እንደቀጠለ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጦርነት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን የዝቅተኛና መካከለኛ መስመር የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ጥገና ስራ እየተከናወነ መሆኑን የጎንደር ዲስትሪክት ገለፀ፡፡

የዲስትሪክቱ ዳይሬክተር አቶ ሞገስ አበራ ÷ የመስመር ጥገና ሥራው እየተከናወነ የሚገኘው በሶስት አቅጣጫ መሆኑን ገልፀው የመጀመሪው ከሁመራ-ማይካድራ-አብድራፊ-አብረሃጅራ፣ ሁለተኛው ከሁመራ-ባከር-ዳንሻ እና ሶስተኛው ደግሞ ከሁመራ-አዲ ጎሹ የሚገኙ አካባቢዎች ናቸው ብለዋል፡፡

አቶ ሞገስ አሁን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል በኩል እየተከናወነ የሚገኘውን የጥገና ሥራ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የጥገና ስራው እንደተጠናቀቀም አካባቢዎቹ ዳግም የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ መግለፃቸውን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ዳይሬክተሩ በጦርነቱ ምክንያት ከሁመራና ሽረ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ኤሌክትሪክ ያገኙ የነበሩ ሁመራ፣ አዲ ጎሹ፣ አዲ ረመፅ፣ ዳንሻ፣ ከተማ ንጉስ፣ ማይካድራ እና አብዲራፊ፣ አዲሪቃይ፣ ኢንዳባጉና፣ አዲገብሩ ከተሞችና አካባቢዎቻቸው ኃይል ተቋርጦባቸው መቆየቱንም አስታውሰዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.