Fana: At a Speed of Life!

አፍሪካ ለኢንዱስትሪ ልማት መረጋገጥ ትኩረት እንድትሰጥ አቶ ደመቀ መኮንን ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አፍሪካ ለኢንዱስትሪ ልማት መረጋገጥ ትኩረት እንድትሰጥ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አቶ ደመቀ መኮንን ዛሬ ኒጀር ርዕሰ መዲና ኒያሚ በተካሄደው የአፍሪካ ህብረት 17ኛ ልዩ የመሪዎች ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ አፍሪካ በአህጉሩ የኢንዱስትሪ ልማት እንዲስፋፋና የኢኮኖሚ ዕድገት እንዲጨምር መስራት ይኖርባታል ብለዋል።

የኢንዱስትሪ ልማት አፍሪካ የተፈጥሮ ሀብቷን ተጠቅማ እንድትለማና በአፍሪካ ሀገራት መካከል የሚካሄድ ንግድ እንዲስፋፋ አስፈላጊ መሆኑንም ገልፀዋል።

አቶ ደመቀ የኢትዮጵያ መንግስት የኢንዱስትሪ ልማት እንቅስቃሴን በተመለከተ ለስብሰባው ተሳታፊዎች ገለጻ ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ መንግስት የተለያዩ የኢንዱስትሪ ፖለሲዎችን ተግባራዊ በማድረጉ ስኬታማ መሆኑን ጠቅሰው÷ 22 የኢንዱስትሪና የተቀናጀ የግብርናና አንዱስትሪ ፓርኮች መገንባቱን ተናግረዋል።

መንግስት ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ተግባራዊ ማድረጉንና መዋቅራዊ መስናክሎችን በመፍታት ለግል ባለሃብቶች የተመቻቸ የስራ ሁኔታ ለመፍጠር እየሰራ መሆኑንም አብራርተዋል።

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.