Fana: At a Speed of Life!

የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ በ1 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ያስገነባቸውን ኅንጻዎች አቶ ኡሞድ ኡጁሉ መረቁ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ በ1 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ገንብቶ ያጠናቀቃቸውን የግንባታ ፕሮጀክቶች አጠናቆ የክልሉ ርዕሠ-መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በተገኙበት ዛሬ አስመርቋል፡፡

ኀንፃዎቹ የተማሪዎች የመማሪያ ክፍሎችን፣ ማደሪያ ዶርሚተሪዎችን እና ሌሎች መሠረታዊ አገልግሎቶችን ያካተቱ ናቸው ተብሏል፡፡

ኅንፃዎቹ 2 ሺህ 400 ተማሪዎችን ማስተናገድ የሚችሉ 400 የመኝታ ክፍሎች፣  3 ሺህ 200 መማሪያ ክፍሎች ያሏቸው 2 ብሎኮች እንዲሁም  2 ሺህ ተማሪዎችን የሚያስተናግድ  ቤተ መጻሕፍትና 120 ሰዎችን የሚይዝ 300 ክፍሎች ያሉት የመምህራን መኖሪያ ግንባታዎችን ያካተቱ ናቸው።

ከኅንፃዎቹ በተጨማሪ 3 ባለ 1 ሺህ 250 ኪሎ ቮልት አምፒር  ጀነሬተሮች  ቀጥታ የሰብስቴሽን መብራትና 2 ነጥብ 4 ኪሎ ሜትር የውስጥ ለውስጥ  አስፓልት መንገድ ግንባታ ተጠናቆ ለምረቃ  መብቃቱን  የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ኡጁሉ ኦኮክ መናገራቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

አራት ተጨማሪ ብሎኮች እና የግቢ ማስዋብ ሥራዎችም በመሠራት ላይ መሆናቸው ነው የተጠቆመው።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.