Fana: At a Speed of Life!

በምድብ 1 ኔዘርላንድስ እና ኢኳዶር ነጥብ ሲጋሩ ኳታር የመጀመሪያዋ ተሰናባች ሆናለች

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 16 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም ዋንጫው ምድብ 1 ኔዘርላንድስ እና ኢኳዶር ነጥብ ተጋርተው ወጥተዋል።

ሁለቱ ቡድኖች ምሽት 1 ሰአት ላይ ባደረጉት ጨዋታ የዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ፈጣን ጎል ተመዝግባለች።

ጨዋታው አንድ አቻ ሲጠናቀቅ ኮዲ ጋክፖ ለኔዘርላንድስ ኤነር ቫሌንሺያ ደግሞ ለኢኳዶር ጎሎችን አስቆጥረዋል።

ጋክፖ በ5ኛው ደቂቃ ከ4 ሰከንድ ያስቆጠራት ጎልም የኳታሩ የዓለም ዋንጫ ፈጣኗ ጎል ሆና ተመዝግባለች።

ኤነር ቫሌንሺያ ለሃገሩ ያስቆጠራት ጎልም በውድድሩ ሶስተኛው ስትሆን፥ በዓለም ዋንጫ ተሳትፎው ደግሞ በአምስት ጨዋታዎች 6ኛ ጎሉ ሆናለች።

ከዚህ ባለፈም የሀገሩ ኢኳዶር የዓለም ዋንጫ የመጨረሻ ስድስት ጎሎች አስቆጣሪም ሆኗል።

ቫሌንሺያ በጨዋታው መጠናቀቂያ በጉዳት ሳቢያ ከሜዳ ወጥቷል።

በምድቡ ቀደም ብሎ በተደረገ ጨዋታ አፍሪካዊቷ ሴኔጋል አስተናጋጇ ኳታርን 3 ለ 1 አሸንፋለች።

ውጤቱን ተከትሎም አስተናጋጇ ኳታር ከምድቧ የተባረረች ሀገር መሆኗ ተረጋግጧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.