Fana: At a Speed of Life!

17ኛው የአፍሪካ ህብረት ልዩ ጉባኤ በኒጀር ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 16 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 17ኛው የአፍሪካ ህብረት ልዩ ጉባኤ በኒጀር ኒያሚ ተካሄዷል።

በጉባኤው ኢትዮጵያን በመወከል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራ ልዑክ ተሳትፎ አድርጓል።

አቶ ደመቀ በጉባኤው ላይ ከነበራቸው ተሳትፎ ባሻገር ከተለያዩ ሃገራት እንግዶች ጋር ውይይት አድርገዋል።

ከመደበኛ ጉባኤው ጎን ለጎን በተካሄዱ በተካሄዱ ስብሰባዎች ላይ በመሳተፍ ንግግር ማድረጋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

በአፍሪካ ኤሌክትሮኒክስ ግብይት መድረክ ላይ በመገኘት አቶ ደመቀ ባደረጉት ንግግር የወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ የአህጉሪቷ ቀዳሚ ጉዳይ መሆኑን ጠቁመዋል።

በኢንዱስትሪ ልማት ላይ ባተኮረው መድረክ ላይም በአፍሪካ የኢንዱስትሪ ልማትን ለማረጋገጥ በፖሊሲ የተደገፈ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.