Fana: At a Speed of Life!

በዓለም ዋንጫው አርጀንቲና ከሜክሲኮ ወሳኙን ጨዋታ ያደርጋሉ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 17 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኳታሩ የዓለም ዋንጫ ዛሬ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

በዛሬው ውሎ የምድብ ሶስት እና አራት ቡድኖች ሁለተኛ የምድብ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

በምድብ ሶስት አርጀንቲና ከሜክሲኮ እንዲሁም በምድብ አራት ፈረንሳይ ከዴንማርክ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ሆኗል።

በተለይም በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዋ ሳይጠበቅ በሳዑዲ አረቢያ የተሸነፈችው አርጀንቲና ከሜክሲኮ የሚያደርጉት ጨዋታ ትልቅ ትኩረትን ስቧል።

ቀን 7 ሰአት በምድብ 4 ቱኒዚያ ከአውስትራሊያ እንዲሁም 10 ሰአት ላይ ደግሞ በምድብ 3 የሚገኙት ፖላንድ እና ሳዑዲ አረቢያ ይጫወታሉ።

ምሽት 1 ሰአት ላይ በምድብ 4 ፈረንሳይ ከዴንማርክ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ምሽት 4 ሰአት ደግሞ አርጀንቲና ከሜክሲኮ ወሳኙን ጨዋታ የሚያደርጉ ይሆናል።

አምስተኛ የዓለም ዋንጫ ተሳትፎውን እያደረገ ያለው የአርጀንቲናው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ፥ በዓለም ዋንጫው ባደረጋቸው 20 ጨዋታዎች 7 ጎሎችን በስሙ አስመዝግቧል።

ዛሬ ምሽት 4 ሰአትም የመጨረሻው በሆነው የዓለም ዋንጫ ወሳኝ የሆነውን 21ኛ የዓለም ዋንጫ ጨዋታውን ያደርጋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.