Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሶማሌ ክልል 110 የውሃ ፓምፖችን ለገሰ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር ማስተዋወቂያ መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡
 
በመርሐ ግብሩ የመስኖና ቆላማ አካባዎች ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሃመድ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ተገኝተዋል፡፡
 
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ÷ ክልሉ ያጋጠመውን ድርቅ ተቋቁሞ ዛሬ ለሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር በመድረሱ እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
 
ኢትዮጵያ እዚህ የደረሰችውና ለዛሬ የበቃችው የደም ዋጋ ተከፍሎላት ቢሆንም ነፃነቷ የጸና እንዲሆን ከድህነት በፍጥነት ሊያላቅቅ የሚችል ጠንካራ ኢኮኖሚ መገንባት ስንችል ነው ብለዋል፡፡
 
ክልሉ ያለውን የተፈጥሮ ፀጋና አቅም በትክክል መጠቀም ከተቻለ ክልሉ መላውን ኢትዮጵያ የመመገብ አቅም አለው ሲሉም ገልፀዋል፡፡
 
በተለይም በወተት ምርት መድሃኒትነት ያለውን የግመል ወተት ምርት በማምረት ለሌሎችም መትረፍ የሚችል ክልል መሆኑን ተናግረዋል፡፡
 
አዲስ አበባ የሁላችንም ከተማ እንደመሆኗ ለክልሉ አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ምርቶች ገበያ እንድትሆን አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚደረግም አረጋግጠዋል፡፡
 
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የክልሉ የሌማት ትሩፋት ፕሮግራም እንዲጠናከር 110 ያህል የውሃ ፓምፖችን ድጋፍ በማድረግ ለክልሉ ማስረከቡንም ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.