Fana: At a Speed of Life!

ቻይና ለዓለም ሰላም እና መረጋጋት ከሰሜን ኮሪያ ጋር በቅንጅት ለመስራት ቁርጠኛ ናት- ሺ ጂንፒንግ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና ለዓለም ዘላቂ ሰላም እና ልማት ከሰሜን ኮሪያ ጋር በቅንጅት ለመስራትቁርጠኛ ናት ሲሉ ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ገለጹ፡፡

የቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ሰሜን ኮሪያ ታይቶ ባማይታወቅ ሁኔታ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሚሳኤሎች ማስወንጨፏን ተከትሎ ለሀገሪቱ መሪ ኪም ጆንግ ኡን መልዕክት ልከዋል፡፡

በመልዕክታቸውም ቤጂንግ ለቀጣናው ብሎም ለዓለም ዘላቂ ሰላም፣ መረጋጋት፣ ልማትና ብልጽግና ከፒዮንግያንግ ጋር በቅንጅት ለመስራት ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል፡፡

ዓለም በሚገርም ሁኔታ አዳዲስ ለውጦችን እያስተናገደች ነው ያሉት ሺ ጂንፒንግ ÷ሀገራቸው በተለያዩ ዘርፎች ከሰሜን ኮሪያ ጋር በትብብር ለመስራት እንደምትፈልግ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

ሰሜን ኮሪያ በተለይም በቅርቡ ለሙከራ በሚል ያስወነጨፈቻቸው አህጉር አቋራጭ ባላስቲክ ሚሳኤሎች አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያን ጨምሮ ቀጣናው ሥጋት ላይ መውደቁ ተመላክቷል፡፡

ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ከቡድን 20 አባል ሀገራት ስብሰባ ጎን ለጎን ከአሜሪካ አቻቸው ጆ ባይደን ጋር ባደረጉት ውይይት÷ ፒዮንግያንግ በቀጣይ መሰል ጠብ አጫሪ ድርጊቷን እንደምታቆም እምነታቸው እንደሆነ መናገራቸው ይታወሳል፡፡

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በበኩላቸው ÷ቻይና ለሰሜን ኮሪያ ወሳኝ የኢኮኖሚ አጋር በመሆኗ ሀገሪቱ ከአላስፈላጊ ድርጊቷ እድትቆጠብ ጫና እንድታደርግ መጠየቃቸውንም አልጀዚራ በዘገባው አስታውሷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.