Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴሩ ለሶማሌ ክልል 400 የውሃ መሳቢያ ፓምፖችን ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር በሶማሌ ክልል ለሚካሄደው የግብርና ስራ የሚያግዙ 400 የውሃ መሳቢያ ፓምፖችን ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉን የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አይሻ ሙሃመድ በሌማት ትሩፋት ማስተዋወቂያ መርሐ ግብር ላይ ተገኝተው ለክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ አስረክበዋል፡፡

በተጨማሪም ማንቶ የተሰኘው የውሃ መሳቢያ ፓምፕ ማምረቻ ፋብሪካ ባለቤቶች 10 የውሃ ፓምፖችን ለክልሉ በድጋፍ አበርክተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.