Fana: At a Speed of Life!

170 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ170 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዙን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

ኮሚሽኑ ከህዳር 9 እስከ 15 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረገው ክትትል ነው 137 ነጥብ 2 ሚሊየን የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች እና 33 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ የወጪ በድምሩ ከ170 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎችን ያያዘው፡፡

ከተያዙት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሃኒት፣ ተሽከርካሪዎች፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ የጦር መሳሪያዎች፣ አደንዛዥ እጾች እና የምግብ ዘይት እንደሚገኙበት ተገልጿል፡፡

የገቢ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ረገድ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዙት ሞያሌ፣ ድሬድዋ እና ኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ ቤቶች÷ በቅደም ተከተላቸው 36 ነጥብ 8 ሚሊየን፣ 24 ነጥብ 5 ሚሊየን 15 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዛቸው ተመላክቷል፡፡

የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 31 ግለሰቦች እና 18 ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.