Fana: At a Speed of Life!

የሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ 34 በመቶ ደረሰ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ስራ 34 በመቶ መድረሱ ተገለጸ፡፡
በፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር የተመራ ልዑክ በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ እየተገነባ የሚገኘውን የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ሒደት ጎብኝቷል፡፡
ግንባታውን አያከናወነ የሚገኘው ተቋራጭ ድርጅት ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ሳምሶን በላቸው÷አሁን ላይ የአውሮፕላን ማረፊያው ግንባታ ሒደት 34 በመቶ መድረሱን ተናግረዋል፡፡
የግንባታው የወሰን ስከበር ስራዎች አለመጠናቀቃቸውን የገለጹት ስራ አስኪያጁ ÷ እነዚህ ስራዎች በተያዘላቸው ጊዜ ቢጠናቀቁ ኖሮ ግንባታውን 53 በመቶ ማድረስ ይቻል እንደነበር አመልክተዋል፡፡
አቶ አገኘሁ ተሻገር ÷ የግንባታ ስራው ያሉበት ችግር ተቀርፎ ፈጥኖ እንዲጠናቀቅ የፌደሬሽን ምክር ቤቱ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል፡፡
የሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፍያ ግንባታ መሰረት ድንጋይ በ2013 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መቀመጡ የሚታወስ ነው።
በ926 ሚሊየን ብር ወጪ የተጀመረው የሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፊያ 4 ኪሎ ሜትር ርዝመትያለው ሲሆን÷ የግንባታ ስራውን በ2 ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ታቅዶ ነው ነበር፡፡
በአለማየሁ መቃሳ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.