Fana: At a Speed of Life!

“የኢንተርኔት አባት” በመባል የሚጠሩት ቪንቶን ግሬይ ሰርፍ አዲስ አበባ ገብተዋል

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) “የኢንተርኔት አባት” በመባል የሚጠሩት ቪንቶን ግሬይ ሰርፍ ዓለም አቀፉን የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባኤ ለመታደም አዲስ አበባ ገብተዋል።

ቪንቶን ግሬይ ሰርፍ አዲስ አበባ ሲደርሱ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ኢትዮጵያ የምታስተናግደው ዓለም አቀፉ የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባኤ ከሕዳር 19 እስከ 23 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡

በጉባኤው ከ2 ሺህ 500 በላይ እንግዶች የሚሳተፉ ሲሆን÷ ከ2 ሺህ በላይ የውጭ ሀገር እና የሀገር ውስጥ እንግዶች መመዝገባቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.