Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች አጎራባች ዞኖች የሰላምና የልማት ኮንፈረንስ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልሎች አጎራባች ዞኖች የሰላምና የልማት ኮንፈረንስ በሶማሌ ክልል ሊባን ዞን ጉሬ ዳሞሌ ወረዳ ተካሂዷል።

በመድረኩ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወሉ አብዲ እና የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ዑስማን እንዲሁም የባሌ ዞን እና ሊበን ዞን አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል ጅብሪ እና በሶማሌ ክልል በጉራ-ዳሞ ኦሌ ወረዳዎች የሚኖሩ የኦሮሞና ሶማሌ ወንድማማች ሕዝቦች መካከል ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባት ከሁለቱ ሕዝቦች የተወጣጡ የሃገር ሽማግሌዎች፣ ምሁራንና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት ከስምምነት መደረሱ ተገልጿል፡፡

በሶማሌና በኦሮሞ ሕዝቦች መካከል ለዘመናት የነበረው ወንድማማችነትና አብሮነት የበለጠ እንዲጠናከር የሀገር ሽማግሌዎች የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።

በሰላምና ልማት ኮንፈረንሱ ላይ የተሳተፉ ሁሉም አካላት በአለመግባባቱ የደረሰውን ጉዳት ይቅር በመባባል የተደረሰውን ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ እእንደሚሰሩ መናገራቸውን የሶማሌ ክልል ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.