Fana: At a Speed of Life!

17ኛው የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 17ኛው የኢትዮጵያ የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል፡፡

“ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችን ለዘላቂ ሰላማችን” በሚል መሪ ሐሳብ በተከበረው በዓል ላይ÷ የተለያየ ብሔር ብሔረሰብ ተወካዮች ባህላዊ ትርዒት አቅርበዋል፡፡

በበዓል አከባበሩ ላይ÷ የክልሉ ምክርቤት ምክትል አፈ ጉባዔ ዓለምነሽ ይባስ፣ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጌታሁን አብዲሳን ጨምሮ በየደረጃው ያሉ አመራሮች እና ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።

ወይዘሮ አለምነሽ ይባስ ባደረጉት ንግግር÷ ዕለቱ ለዲሞክራሲያዊ ሕገ መንግስታችን መከበር ያለንን ቁርጠኝነት የምናሳይበት እና ሀገራዊ አንድነታችንን የምናጠናክርበት ነው ብለዋል፡፡

ሰላምን በማስጠበቅ እና ሙስናን በመታገልየተጀመረውን የልማት ጉዞ ለማስቀጠል ሁሉም በተሰማራበት ዘርፍ አርዓያነት ያለው ተግባር ሊፈጽም ይገባል ብለዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.