Fana: At a Speed of Life!

ከአላማጣ- ቢሶበር ያሎ ከልዋን የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ጥገና ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጉዳት ደርሶበት የነበረው ከአላማጣ- ቢሶበር ያሎ ከልዋን ድረስ ያለው የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ጥገና ሥራ መጠናቀቁን የአፋር ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

የአገልግሎቱ ሥራ አስፈፃሚ ያሲን ዓሊ እንደገለጹት÷ ከአላማጣ -ቢሶበር ያሎ ከልዋን ያለው የመካከለኛ እና ዝቅተኛ መስመር እንዲሁም የትራንስፈርመር ጥገና ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል፡፡

በቅርቡም ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል ዳግም ወደ አገልግሎት እንደሚመለስ መናገራቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መረጃ ያመላክታል፡፡

ከመቀሌና ውቅሮ ሰብስቴሽኖች የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያገኙት በኪልበቲ ረሱ ስር የሚገኙ ወረዳዎች ጥገና ለማካሄድ የኢንስፔክሽን ሥራ እየተሠራ መሆኑን ጠቅሰው÷ለጥገና የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን በማሟላት ወደሥራ እንደሚገባ አረጋግጠዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.