Fana: At a Speed of Life!

ዲፕሎማቶች ወቅቱን ያገናዘበ፣ በብልሀት የሚመራ የዲፕሎማሲ ሥራ ሊያከናውኑ ይገባል- አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በተለያዩ የዲፕሎማሲ ጫናዎች ውስጥ መሆኗን በመገንዘብ ዲፕሎማቶች ወቅቱን ያገናዘበ፣ በብልሀት የሚመራ የዲፕሎማሲ ሥራ ሊያከናውኑ እንደሚገባ አቶ ደመቀ መኮንን ተናገሩ፡፡

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ዲፕሎማሲ ያላት ተሳትፎ ላይ አተኩሮ በአፍሪካ የልህቀት ማዕከል ለሦስት ሣምንታት ሲሰጥ የሰነበተው ስልጠና ተጠናቋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ እንደገለጹት÷ ኢትዮጵያ በተለያዩ የዲፕሎማሲ ጫናዎች ውስጥ መሆኗን በመገንዘብ ዲፕሎማቶች ወቅቱን ያገናዘበ፣ በብልሀት የሚመራ የዲፕሎማሲ ሥራ ሊያከናውኑ ይገባል፡፡

ስልጠናው ዲፕሎማቶቹ አሁናዊ የሆነውን ተለዋዋጭ፣ ተገማች ያልሆነውን እና የተወሳሰበውን የዓለም ስርዓት በማንበብ የሀገራቸውን እውነት እና ጥቅም ማስከበር እንዲችሉ ያግዛል ብለዋል፡፡

ስልጠናው ሀገራዊ ተልዕኮውን በአግባቡ የሚወጣ ዲፕሎማት ለመፍጠር የሚያግዝ መሆኑም ተገልጿል፡፡

በስልጠናው ላይ÷ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ፕሬዚዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ስልጠና መስጠታቸው እና ልምዳቸውን ማካፈላቸው ይታወቃል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.