Fana: At a Speed of Life!

ኦሮሚያ ባንክ በዓለም አቀፍ የባንክ ሥራዎች ከ279 ሚሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ አገኘሁ አለ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኦሮሚያ ባንክ በ2014 ዓ.ም በዓለም አቀፍ የባንክ ሥራዎች ከ279 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ማግኘቱን አስታውቋል፡፡

ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ55 በመቶ ዕድገት ማሳየቱ ነው የተገለጸው፡፡

የኦሮሚያ ባንክ የባለአክሲዮኖች 13ኛ ጠቅላላ ጉባዔ እና 4ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ እየተካሄደ ነው፡፡

በጉባዔው እንደተገለጸው÷ ባንኩ በ2014 ዓ.ም ከግብር በፊት 1 ነጥብ 52 ቢሊየን ብር ትርፍ አግኝቷል፡፡

የአክሲዮን ገቢ 307 ብር መሆኑ እና የተገኘው ትርፍ ካለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር 13 ነጥብ 7 በመቶ ጭማሪ ማስመዝገቡ ተገልጿል።

የኦሮሚያ ባንክ የዳሬክተሮች ቦርድ ኃላፊ ገመቹ ዋቅቶላ ባንኩ በበጀት ዓመቱ አጠቃላይ ገቢ 52 ቢሊየን ብር ማስመዝገቡን ተናግረዋል፡፡

ይህም ከ2014 ዓ.ም በፊት ከነበረው በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ24 ነጥብ 8 በመቶ ብልጫ እንዳለው ተናግረዋል።

ባንኩ ያሉትን ቅርንጫፎች ወደ 400 ማሳደጉንም ገልጸዋል፡፡

በማህሌት ተክለብርሃን
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.