Fana: At a Speed of Life!

በዓለም ዋንጫ አፍሪካዊቷ ሞሮኮ ወሳኝ የምድብ ድሏን አስመዘገበች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም ዋንጫ አፍሪካዊቷ ሞሮኮ ቤልጂየምን 2 ለ 0 በማሸነፍ የመጀመሪያ ድሏን አስመዝግባለች፡፡

በጨዋታው ብርቱ ተፎካካሪ ሆና የቀረበችው የሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር ሞሮኮ ከእረፍት መልስ አብዱልሃሚድ ሳብሪል እና ዛካሪያ አቡክላል ባስቆጠሯቸው ጎሎች ቤልጂየምን በማሸነፍ ወሳኝ ድል አስመዝግባለች፡፡

ሞሮኮ ከሴኔጋል በመቀጠል በዓለም ዋንጫው ማሸነፍ የቻለች አፍሪካዊት ሀገር ስትሆን ከምድቡ አራት ነጥብ በመያዝ ከወዲሁ የማለፍ እድሏን አስፍታለች፡፡

ቤልጂየም በምድቡ ሶስት ነጥብ ያላት ሲሆን÷ ከምድቡ ለማለፍ ቀጣይ ጨዋታዎችን የምትጠበቅ ይሆናል፡፡

በዚሁ የምድብ ስድስት ጨዋታ ምሽት አንድ ሰዓት ክሮሺያ ከካናዳ ጨዋታቸውን ሲያደርጉ ምሽት 4 ሰዓት ደግሞ በምድብ አምስት ስፔን ከጀርመን የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው፡፡

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.