Fana: At a Speed of Life!

በነገው እለት በመዲናዋ 13 ዋና ዋና መንገዶች ላይ የፀረ ተዋህስ መድሃኒት ርጭት ይደረጋል

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 19 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ በሚገኙ 13 ዋና ዋና መንገዶች ላይ የፀረ ተዋህስ መድሃኒት ርጭት በነገው እለት ይደረጋል።

በተመረጡት መንገዶች ላይ የመከላከያ መድሃኒት ርጭት የማድረግ ስራ የሚከናወን ይሆናል።

በዚህ መሠረት

-መስቀል አደባባይ – ቦሌ ፣

-መስቀል አደባባይ – ጦር ሃይሎች ፣

-መስቀል አደባባይ – 6 ኪሎ ፣

-ከመስቀል አደባባይ – ጎተራ – ሳሪስ

-ከመስቀል አደባባይ – መገናኛ ፣

-ከብሄራዊ – ሜክሲኮ፣

-ከሱፐር ማርኬት – ካዛንችስ – ኡራዔል ፣

– ከምኒልክ አደባባይ – አምባሳደር – መስቀል አደባባይ፣

– ከምኒልክ አደባባይ – ፓስተር፣

– ከምኒልክ አደባባይ – 4 ኪሎ – መገናኛ፣

– ከምኒልክ አደባባይ – 6 ኪሎ ፣

– ከምኒልክ አደባባይ – አውቶብስ ተራ ፣

– ከምኒልክ አደባባይ – ተክለሃይማኖት

ያሉት መንገዶች የመድሀኒት ርጭት የሚካሄድባቸው ይሆናል።

የፀረ – በሽታ አምጭ ተዋህስ መድሀኒት ርጭት የሚካሄድባቸው መንገዶች 41 ኪሎ ሜትር የሚሽፍኑ ናቸው።

በዚህ ምክንያት የተጥቀሱት መንገዶች ከጠዋቱ 2 ሰዓት እስከ ቀኑ 6 ሰዓት ድረስ ለአገልግሎት ዝግ የሚሆኑ ይሆናል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.