Fana: At a Speed of Life!

17ኛው ዓለም አቀፉ የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባዔ በአዲስአበባ መካሔድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት የሚካሔደው 17ኛው ዓለም አቀፍ የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባዔ ዛሬ መካሔድ ጀምሯል፡፡

ለአምስት ተከታታይ ቀናት የሚቆው ጉባዔው÷ አዲስ አበባ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ ነው እየተካሔደ የሚገኘው፡፡

የጉባዔው ዋናው መከፈቻ በነገው እለት እንደሚካሄድ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በጉባዔው ለመሳተፍም÷ ከተለያዩ ሀገራት እንግዶች አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

በዚሁ መሠረት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የቴክኖሎጂ ጉዳዮች ከፍተኛ ልዑክ አማንዲፕ ሲንጊህ ጊሊ እና የማላዊ የኢንፎርሜሽንና ዲጂታላይዜሽን ሚኒስትር እና የመንግሥት ቃል አቀባይ ጎስፔል ካዛኮ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

እንግዶቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

አማንዲፕ ሲንጊህ ጊሊ የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የቴክኖሎጂና ዲጂታል ትብብር ከፍተኛ ልዑክ ናቸው።

በተመሳሳይ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳዮች ምክትል ዋና ጸሐፊ ሊ ጁንሁዋ እና የፓፓዋ ኒው ጊኒ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ቲሞቲ ማሲዩ በጉባዔው ለመሳተፍ አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል፡፡

በጉባኤው ለመሳተፍ ከተለያዩ ሀገራት ከ3 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች ተመዝግበዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.