Fana: At a Speed of Life!

ዩኒሴፍ ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለውኃ ተቋማት ጥገና የሚውል ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ የሕጻናት አድን ድርጅት (ዩኒሴፍ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በፀጥታ ችግር ለወደሙ የውኃ ተቋማት ጥገና የሚውል ከ9 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ድጋፍ አደረገ፡፡

ዩኒሴፍ በፀጥታ ችግር የወደሙ 453 የውኃ ተቋማትን መጠገን የሚያስችል 9 ሚሊየን 366 ሺህ 60 ብር ግምት ያላቸው የአስቸኳይ ጊዜ የውኃ መለዋወጫ ቁሳቁስ ለክልሉ ውኃና ኢነርጂ ልማት ቢሮ አስረክቧል፡፡

ድጋፉ የውኃ ተቋማትን መልሶ በመጠገን ለህብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ ያግዛል መባሉን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.