Fana: At a Speed of Life!

ሰላም የጋራ አጀንዳና መዳረሻችን ነው – አቶ ብናልፍ አንዷለም

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 19 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገር አቀፍ የሰላም ምክር ቤት መመስረቻ ጉባኤ እየተካሄደ ነው፡፡
 
በምስረታ ጉባኤው መልዕክት ያስተላለፉት የሰላም ሚኒስትሩ ብናልፍ አንዷለም÷ ሰላማዊ ሀገር ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ምክር ቤቱ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ገልጸዋል
 
ምክር ቤቱ የጋራ አጀንዳ፣ የጋራ መንገድና መዳረሻችን ለሆነው ሰላም እውን መሆን ቃል ኪዳን የምንገባበትና ማህበራዊ ውል የምንፈጽምበት መድረክ ይሆናል ብለዋል።
 
ዛሬ የሚመሰረተው ብሔራዊ የሰላም ምክር ቤት ሶስት መሰረታዊ ውጥኖችን ለማሳካት እንደሚሰራም ነው የተገለጸው፡፡
 
ሰላም ከእያንዳንዱ ግለሰብ የሚጀምር መሆኑን ዜጎች ሁሉ እንዲገነዘቡት ማስቻል፣ በማህበረሰብ ደረጃ በሰለጠነ መንገድ የሰላም ግንባታን ማሳካትና ሀገራዊ የሰላም ግንባታ ተግባራዊነት ላይ አተኩሮ ይሰራል ተብሏል።
 
የዚህ ስራ ግብ የምክር ቤቱን ምስረታ እውን ማድረግ ሳይሆን በዚህ የጋራ መሰባሰቢያ አማራጭ በኩል የሚፈለገውን የሀገር ሰላም ማረጋገጥ መቻል እንደሆነም ተመላክቷል።
 
በበርናባስ ተስፋዬ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.