Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ እና ጂቡቲ ሰላም አስከባሪ ኃይሎች የጥምር ውጊያ ልምምድ አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 19 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአትሚስ ሴክተር አራት 7ኛ ዙር ሰላም አስከባሪ ሃይል ከጂቡቲ ሰላም አስከባሪ ኃይል ጋር ግዳጅን መሰረት ያደረገ የጥምር ውጊያ ልምምድ አድርገዋል፡፡

የሁለቱ ሀገራት የሰላም አስከባሪ ኃይሎች የጋራ ጥምር ውጊያ ልምምድ ማድረጋቸው ቀጣይ የሚያጋጥሙ ግዳጆችን በተገቢው መንገድ ተናቦ ለመፈጸም ሚናው የጎላ ነው ሲሉ የሴክተሩ ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ሹመት ጠለለው ተናግረዋል።

ምክትል አዛዡ እንዳሉት ልምምዱ አልሸባብ አልፎ አልፎ የሚፈፅማቸውን ትንኮሳዎች በመመከት መደምሰስ እንዲቻል የሚረዳ ከመሆኑም በላይ የኢትዮጵያን እና የጂቡቲን ወታደሮች አንድነት ያጠናክራል፡፡

ከልምምዱ በኋላ ሰላም አስከባሪ አባላቱ በሰጡት አስተያየት የመስክ ልምምዱ በተግባር ላይ የተደገፈ በመሆኑ ወታደራዊ ቁመናን ለመፈተሸ እና ከጂቡቲ ሃይል ጋር ጥምረት በመመስረት አልሸባብን ለመደምሰስ የሚያግዝ ነው ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ሰላም ከእያንዳንዱ ግለሰብ የሚጀምር መሆኑን ዜጎች ሁሉ እንዲገነዘቡት ማስቻል፣ በማህበረሰብ ደረጃ በሰለጠነ መንገድ የሰላም ግንባታን ማሳካትና ሀገራዊ የሰላም ግንባታ ተግባራዊነት ላይ አተኩሮ ይሰራል ተብሏል።

የዚህ ስራ ግብ የምክር ቤቱን ምስረታ እውን ማድረግ ሳይሆን በዚህ የጋራ መሰባሰቢያ አማራጭ በኩል የሚፈለገውን የሀገር ሰላም ማረጋገጥ መቻል እንደሆነም ተመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.