Fana: At a Speed of Life!

የሊጉ መርሐ ግብሮች እና ተስተካካይ ጨዋታዎች በድሬዳዋ መካሄዳቸውን ይቀጥላሉ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከ11ኛ እስከ 13ኛ ሳምንት ያሉ ጨዋታዎችን ጨምሮ ተስተካካይ ጨዋታዎች በድሬዳዋ መካሄዳቸውን ይቀጥላሉ፡፡

የ2015 ዓ.ም ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከ1ኛ እስከ 5ኛ ሳምንት በባህር ዳር ከተማ የተከናወነ ሲሆን ከ6ኛ እስከ 10ኛ ሳምንት ያሉ ጨዋታዎች በድሬደዋ ከተማ እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል።

በቀጣይም ከ11ኛ ሳምንት በኋላ ያሉትን እና ተስተካካይ ጨዋታዎች መርሐ ግብርን በተመለከተ ውድድሩ ለቻን የአፍሪከ ዋንጫ የሚቋረጥበትን ጊዜ እና የቀጣይ አስተናጋጅ ከተማን ገምግሞ ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህ መሰረት ከ11ኛ እስከ 13ኛ ሳምንት ያሉ 22 ጨዋታዎች እና 5 ተስተካካይ ጨዋታዎች በድሬዳዋ ከሕዳር 25 እስከ ታህሳስ 17 ቀጥለው የሚካሄዱ ይሆናል።

ከሱፐር ስፖርት ጋር ቀድሞ በተካሄደ ውይይት መሰረት ከ14ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ጀምሮ በአዳማ ከተማ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በቀጣይ በሚወጣ ፕሮግራም የሚካሄዱ መሆኑን ሊግ ኩባንያው አስታውቋል፡፡

የ10ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ የሚጀመሩ ሲሆን መቻል ከኢትዮ ኤሌክትሪክ 10 ሰዓት እንዲሁም ኢትዮጵያ መድን ከሐዋሳ ከተማ ምሸት 1 ሰዓት ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.