Fana: At a Speed of Life!

ህብረ ብሔራዊ አንድነታችን ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል -ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ህብረ ብሔራዊ አንድነታችን ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ገለጹ፡፡
 
በክልሉ17ኛው የብሔር ብሔረሰቦች በዓል ቀን ህብረ ብሔራዊ አንድነታችን ለዘላቂ ሠላም በሚል መሪ ቃል በቦንጋ ከተማ እየተከበረ ነው።
 
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ÷ ክብረ በዓሉ የህዝቦችን ታሪክ፣ባህል ፣ቋንቋ እና ህብራዊ አንድነትን በማንጸባረቅ ጉልህ ሚና አለው ብለዋል።
 
በዓሉሲ ከበርም እርስ በርስ በመከባበርና በመተሳሰብ ብሎም የባህል ልውውጦችን በማድረግ መሆኑን እንደሚገባው ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ አሳስበዋል።
 
ኢትዮጵያዊ የሆነውን የጋራ እሴት የምናጎላበት አንዱ ለሌላው አለኝታ የሚሆንበት እንዲሆንም ተናግረዋል ።
 
የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ወንድሙ ኩርታ በበኩላቸው÷ ህገ መንግሥቱ ብዝሃነትን በማስተናገድ ሀገራዊ አንድነትን በማጠናከር መሠረት እንደጣለ መጠቆማቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
16ኛው የብሔር ብሔረሰቦች በዓል ቀን ሲከበር ሀገር በጭንቅ ውስጥ ሆና የተፈተነችበት ወቅት መሆኑን ያወሱት ዋና አፈ ጉባኤው÷ በጭንቀት ውስጥ ሆና ህብረ ብሔራዊ አንድነትን በማጠናከር ሀገራዊ የልማት ዕቅድ ግቦች ዕውን መሆን የቻለበት እንደሆነም ገልጸዋል።
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.