Fana: At a Speed of Life!

አዝናኙ የካሜሩን እና የሰርቢያ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ድራማዊ ትዕይንት ያስተናገደው የካሜሩን እና የሰርቢያ ጨዋታ 3 አቻ ተጠናቋል፡፡

በጨዋታው ካሜሩን በሰርቢያ ብልጫ ተወስዶባት 3 ለ 1 ስትመራ ብትቆይም በቪንሰንት አቡበከር እና ቺፖ ሞቲንግ ሁለት ጎሎች ታግዛ አቻ መሆን ችላለች።

የካሜሩንን ጎሎች ጄን ካሴሌቶ፣ ቪንሰንት አቡበከር እና ቺፖ ሞቲንግ ሲያስቆጥሩ የሰርቢያን ጎሎች ደግሞ ስትራኒያ ፓቭሎቪች፣ ሳቪች እና አሌክሳንደር ሚትሮቪች አስቆጥረዋል፡፡

ከጨዋታው ቀደም ብሎ ለኢንተር ሚላን የሚጫወተው ግብ ጠባቂው አንድሬ ኦናና ከአሰልጣኙ ጋር ባለመግባባቱ ምክንያት የቡድኑን ካምፕ ለቆ ወጥቷል።

በምድቡ ቀደም ብሎ ሲል በተደረጉ ጨዋታዎች ካሜሩን በስዊዘርላንድ 1 ለ 0 ስትሸነፍ ሰርቢያ ደግሞ በብራዚል 2 ለ 0 መሸነፏ የሚታወስ ነው፡፡

በምድቡ የመጨረሻ መርሐ ግብር ካሜሩን ከብራዚል እንዲሁም ሰርቢያ ከስዊዘርላንድ ይገናኛሉ።

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.