Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ ኢስዋቲኒ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላሳየችው ሚዛናዊ አቋም ምስጋና አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከኢስዋቲኒ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቱሊሲል ድላድላ ጋር ተወያይተዋል፡፡
 
በውይይታቸውም በኢትዮጵያ እና ኢስዋቲኒ የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
 
አቶ ደመቀ ስለኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ እና በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው የሰላም ስምምነት ዙሪያ ለኢስዋቲኒ አቻቸው ገለጻ አድርገዋል፡፡
 
የኢትዮጵያ መንግስት በስምምነቱ መሰረት ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ለተግባራዊነቱ በትኩረት እየሠራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
 
ኢስዋቲኒ ኢትዮጵያ ችግር ውስጥ ባለችበት ወቅት ላሳየችው ሚዛናዊ እና የማይናወጥ አቋምም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
 
የኢስዋቲኒ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቱሊሲል ድላድላ በበኩላቸው ÷ ለተደረሰው የሰላም ስምምነት ለኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
 
ለሰላም ስምምነቱ ተግባራዊነትም ኢስዋቲኒ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል፡፡
 
ኢስዋቲኒ ከኢትዮጵያ ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነት የጋራ ጥቅምን መሰረት ባደረገ መልኩ አጠናክሮ ለመስቀጠል ፍላጎት እንዳላትም አስገንዝበዋል፡፡
 
ሚኒስትሮቹ ሀገራቱ በጋራ ለመስራት እና ያላቸውን የሁለትዮሽ ግንኙነትና ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ስምምነት ላይ መድረሳቸውንም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.