Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የአፍሪካ፣ ካሪቢያንና ፓሲፊክ ሀገራት ድርጅት ጉባዔ ላይ እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በቤልጂየም ብራሰልስ እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ፣ ካሪቢያንና ፓሲፊክ ሀገራት ድርጅት ጉባዔ ላይ እየተሳተፈች ነው፡፡

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው በ115ኛው የአፍሪካ፣ ካሪቢያንና ፓሲፊክ ሀገራት ድርጅት ጉባዔ ላይ የኢትዮጵያን አቋም ገልጸዋል፡፡

በገለጻቸውም÷ የአፍሪካ፣ ካሪቢያንና ፓሲፊክ ሀገራት ድርጅት ተልዕኮውን በአግባቡ እንዲወጣ ማሻሻያዎችን በተጠናከረ መልኩ ተግባራዊ ማድረግ  እንደሚገባ ኢትዮጵያ ታምናለች ብለዋል፡፡

በቅርቡ በግብጽ ሻርም ኤል ሼክ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ ላይ የተነሱ ቁልፍ ጉዳዮችና ውሳኔዎችም በትኩረት  እንዲተገበሩ መጠየቃቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘም በአየር ንብረት ለውጥ ተጎጂ የሆኑ ሀገራት ተገቢውን የፋይናንስ ድጋፍ እንዲያገኙ የአፍሪካ፣ ካሪቢያንና ፓሲፊክ ሀገራት ድርጅት ድምጽ ሊሆን እንደሚገባ ወይዘሮ ሰመሪታ ተናግረዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.