Fana: At a Speed of Life!

የጎንደር ግብርና ምርምር ማዕከል ምርታማ የቢራ ገብስ ዝርያ አስለቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጎንደር ግብርና ምርምር ማዕከል ”ራስ” የተሰኘ ባለ ስድስት ጠርዝ ምርታማ የቢራ ገብስ ዝርያ ማስለቀቁን አስታውቋል፡፡

ማዕከሉ ለተከታታይ አምስት አመታት ባካሔደው ምርምር አሁን ላይ ካሉ የቢራ ገብስ ዝርያዎች የተሻለ ምርት መስጠት የሚችል ዝርያ ማግኘቱ ተገልጿል፡፡

“ራስ” የሚል ስያሜ የተሰጠው እና ነጭ ቀለም ያለው ዝርያ የቢራ ፋብሪካዎች የሚፈልጉትን ከፍተኛ የጥራት ደረጃ ማሟላቱን የአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት መረጃ ያመላክታል፡፡

በሔክታር ከ 41 እስከ 50 ኩንታል ምርት መስጠት እንደሚችል የተገለጸው ምርቱ÷ በተዘራ ከ 115 እስከ 130 ባሉት ቀናት እንደሚደርስ ተመላክቷል፡፡

ይህም ከተሻሻለው የማወዳደሪያ ዝርያ በ13 ነጥብ 6 በመቶ የምርት ብልጫ ያለውና በበሽታ የመጠቃት እድሉም ዝቅተኛ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.