Fana: At a Speed of Life!

የግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ተግባራዊነትና ዘላቂነት ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ተግባራዊነትና ዘላቂነት ፕሮጀክት የማስጀመሪያ መርሐ ግብር የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡

ፕሮጀክቱ በፈረንጆቹ አቆጣጠር ከጥር 2022 እስከ 2025 የሚቆይ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ፕሮጀክቱ ለግብርና ማቀነባበር ሴክተር ልማት፣ ለአራቱ የተቀናጀ ግብርና ማቀነባበሪያ ፓርኮች ሁሉን አቀፍና ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ማድረግ፣ በልዩ ትኩረትም ለምግብ ደህንነትና አቅም ግንባታ እንዲሁም በገጠሩ የሀገሪቱ ክፍል የተሻለ የስራና የኢኮኖሚ እድሎችን ለመፍጠር ያለመ መሆኑን የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሚልኬሳ ጃገማ ተናግረዋል፡፡

በፈረንጆቹ አቆጣጠር ታህሳስ 2021 በኢትዮጵያ መንግስትና በተባበሩት መንስግታት የልማት ድርጅት መካከል የተፈረመው ይህ ፕሮጀክት አጠቃላይ በጀቱ 2 ነጥብ 065 ሚሊየን ዩሮ ነው ተብሏል፡፡

ፕሮጀክቱ የጣልያን የልማት ትብብር ኤጀንሲ ውጤት ሲሆን አላማውም የፓርኮቹን ሀገር አቀፋዊ እና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ማሳደግ መሆኑን መጠቆሙን ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.